Google Chrome ፈጣን፣ ልለመጠቀም ቀላል እእና ደህንነቱ የተጠበቀ የድር አሳሽ ነው። ለAndroid የተነደፈው Chrome ግላዊነት የተላበሱ የዜና ዘገባዎችን፣ ወደ ተወዳጅ ጣቢያዎችዎ የሚወስዱ ፈጣን አገናኞችን፣ ውርዶችን እና አብሮገነብ Google ፍለጋን እና Google ተርጉምን ያመጣልዎታል። በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ በሚወዱት ተመሳሳዩ የChrome ድር አሳሽ ተሞክሮ ለመደሰት አሁን ያውርዱ።
በፍጥነት ያስሱ እና ያነሰ ይተይቡ። ሲተይቡ በቅጽበት ከሚመጡ ግላዊነት የተላበሱ የፍለጋ ውጤቶች ይምረጡ እና ከዚህ ቀደም የተጎበኙ ድረ-ገጾችን በፍጥነት ያስሱ። በራስ-ሙላ ቅጾችን በፍጥነት ይሙሉ።
ማንነት የማያሳውቅ ሁነታ። ታሪክዎን ሳያስቀምጡ በይነመረቡን ለማሰስ ማንነት የማያሳውቅ ሁነታን ይጠቀሙ። በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ በግል ያስሱ።
Chromeን በሁሉም መሣሪያዎች ላይ ያስምሩት። በመለያ ወደ Chrome ሲገቡ የእርስዎ ዕልባቶች፣ የይለፍ ቃላት እና ቅንብሮች በራስ-ሰር በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ ይሰምራሉ። ሁሉንም መረጃዎ ከእርስዎ ስልክ፣ ጡባዊ ወይም ላፕቶፕ ሆነው ያለምንም እንከን መድረስ ይችላሉ።
ሁሉንም የሚወዱት ይዘት፣ አንዴ መታ በማድረግ ብቻ የሚገኙ። Chrome ፍጥነቱ ለGoogle ፍለጋ ብቻ አይደለም፣ ሁሉም የሚወዱት ይዘት መታ በማድረግ የሚገኙበት ርቀት ላይ እንዲሆኑ ተደርጎ የተነደፈ ነው። ከአዲስ የትር ገጽ ሆነው በቀጥታ የሚወዷቸውን የዜና ጣቢያዎች ወይም ማህበራዊ ሚዲያ መታ ማድረግ ይችላሉ። Chrome እንዲሁም በአብዛኛዎቹ ድረ-ገጾች ላይ የ«ለመፈለግ መታ ያድርጉ» ባህሪ አለው። እርስዎ በሚዝናኑበት ገጽ ላይ እንደሆኑ የGoogle ፍለጋን ለመጀመር ማናቸውንም ቃል ወይም ሐረግ ላይ መታ ማድረግ ይችላሉ።
ስልክዎን በGoogle የጥንቃቄ አሰሳ ይጠብቁት። Chrome አብሮገነብ የGoogle ጥንቃቄ አሰሳ አለው። ወደ አደገኛ ጣቢያዎች ለማሰስ ወይም አደገኛ ፋይሎችን ለማውረድ ሲሞክሩ ማስጠንቀቂያዎችን በማሳየት የስልክዎ ደህንነት የተጠበቀ ሆኖ እንዲቆይ ያደርጋል።
ፈጣን ውርዶች እና ድረ-ገጾችንና ቪዲዮዎችን ከመስመር ውጭጭ መመልከት Chrome ተለይቶ የተሰራ የማውረጃ አዝራር አለው፣ ስለዚህ አንዴ መታ በማድረግ ብቻ ቪዲዮዎችን፣ ስዕሎችን እና መላ ድረ-ገጾችን ማውረድ ይችላሉ። Chrome በተጨማሪ በChrome ውስጥ ሁሉንም እርስዎ ያወረዱትን ይዘት ከመስመር ውጭ ቢሆኑም እንኳ ሊደርሱበት የሚችሉበት የማውረዶች መነሻ አለው።
Google Voice Search. Chrome ሊያናግሩት ትክክለኛ የድር አሳሽ ይሰጠዎታል። ጉዞ ላይ እያሉ ሳይተይቡ ወይም ነጻ እጅ ሆነው መልሶችን ለማግኘት ድምጽዎን ይጠቀሙ። በማንኛውም ጊዜ ድምጽዎን ተጠቅመው በበለጠ ፍጥነት ማሰስ እና መዳሰስ ይችላሉ።
Google ትርጉም አብሮገነብ፦ መላ ድረ-ገጾችን በፍጥነት ያስተርጉሙ። Chrome አንዴ መታ በማድረግ መላው ድር ወደ ቋንቋዎ እንዲያስተረጉሙ የሚያግዘዎ አብሮገነብ Google ትርጉም አለው።
ዘመናዊ ግላዊነት የተላበሱ ምክሮች። Chrome ለፍላጎቶችዎ የተበጀ ተሞክሮን ይፈጥራል። በአዲሱ የትር ገጽ ላይ Chrome በቀዳሚው የአሰሳ ታሪክዎ ላይ ተመስ��ቶ ለእርስዎ የመረጠልዎ ጽሑፎችን ያገኛሉ።