Jump to content

N

ከውክፔዲያ
የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

N / nላቲን አልፋቤት አሥራ አራተኛው ፊደል ነው።

ግብፅኛ
ቅድመ ሴማዊ
ኑን
የፊንቄ ጽሕፈት
ኑን
የግሪክ ጽሕፈት
ኤትሩስካዊ
N
ላቲን
N
D
Greek nu Roman N

የ«N» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ኑን» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የእባብ ስዕል መስለ። የግብጽኛ ተናባቢ ድምጽ ምልክቶች በሚል ጽሕፈት ለዚህ ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ለድምጹ «ጀ» ነበር፤ በሴማውያን ዘንድ ግን «ን» ሆነ። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "" (Ν ν) ደረሰ።

ከ400 ዓክልበ. ግድም በፊት፣ በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት እንዲሁም በጥንታዊ ኢታሊክ አልፋቤት የ«ም» ቅርጽም እንደ «𐌌» ይምሰል እንደ ነበር የ«ን» ቅርጽ ደግሞ እንደ «𐌍» ይጻፍ ነበር። ከዚያስ የ«𐌌» (ም) ቅርጽ እንደ ዛሬ M እንደ ሆነ፣ እንዲሁም የ«𐌍» (ን) ቅርጽ የዛኔ ወደ N ተቀየረ።

በአንዳንድ ቋንቋ በተለይም በእስፓንኛው አልፋቤት ተጨማሪው ፊደል «Ñ» (/ኝ/) ከN የደረሰ ነው። በእስፓንኛ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይህ Ñ የተለየ ፊደል ሆኖ ተቆጥሯል፤ መጀመርያ ግን በጋሊስኛ ከ1220 ዓም ታውቋል።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ነ» («ነሐስ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ኑን» ስለ መጣ፣ የላቲን 'N' ዘመድ ሊባል ይችላል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ N የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።